"በበልግ እርሻ ስራችን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሮቻችንን የኢኮኖሚ አቅም ለማሻሻል እና የኑሮ ውድነት ችግርን ለመቅረፍ እየሰራን ነው:-" አቶ ደስታ ሌዳሞ።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ በዘንድሮ በጀት ዓመት የበልግ እርሻ እንቅስቃሴ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር ጎብኝቷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝታቸው ወቅት የአርሶ አደሩን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል መንግስት አስፈላጊ ግብዓቶችን ከማቅረብ ጀምሮ በባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል በማድረግ የታቀደውን ያህል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችል ሥራ እየሰራ መሆኑን ተናግረው የግብዓት አጠቃቀም ምን እንደሚመስል፣ የምርቱ ቁመና ያለበትን ደረጃ፣ ችግር አጋጥሞ ከሆነ በፍጥነት መፍትሔ ለማበጀት እና አሁን ገና እያመረቱ ያሉ አርሶ አደሮች ደግሞ ውጤታማ ሥራ እንድሰሩ ልምድ የሚወሰድበት ጉብኝትና ግምገማ መደረጉን ገልጸዋል።