Skip to main content
የአቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት
- ከፓርቲው ዓላማዎች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመነሳት የተዘጋጀውን የአቅም ግንባታ ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት ያደረገ በክልሉ ተፈጻሚ የሚሆን የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የፖለቲካ ስራ እቅዶችን ያዘጋጃል፤ ዝርዝር መርሃ ግብር
- አዘጋጅቶ ያስፈፅማል፤
- በክልሉ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው የፖለቲካና የአቅም ግንባታ አደረጃጀቶች ከክልላዊ ዕቅድ ተነስተው ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤ የእቅድ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
- ከፓርቲው ፕሮግራም፣ ስትራቴጂክ እቅድ፣ ከዋና ጽ/ቤትና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የዘርፍ እቅድ በመነሳት የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ስራ እቅዶችን ያዘጋጃል፤ መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
- በክልሉ የሚገኙ የፓርቲው አመራሮችና አባላት የፓርቲውን ራዕይ፣ ዓላማና እቅዶች በብቃት መፈጸም በሚችሉበት ደረጃ ላይ ለማድረስና የፖለቲካና የአመራር ብቃታቸውን የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
- ክልላዊ የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በመቅረጽና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
- የፓርቲው የአቅም ግንባታ ሰነዶች በክልሉ ለሚገኙ አመራሮችና አባላት መድረሳቸውን ይከታተላል፤
- የአመራርና አባላትን የፖለቲካና የመፈፀም አቅም ለመገንባት የሚረዱ ክልላዊ ሰነዶችን በማዘጋጀት ለአመራሩና ለአባላት ግንባታ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
- የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የአመራሮችን እና የአባላት ስልጠና ፍላጎት ይለያል፣ ለሚመለከታቸው አካላት አደራጅቶ ያቀርባል፤
- ፍላጎታቸውን መሰረት በማድረግ ለክልሉ አመራሮችና አባላት ውጤታማ ስልጠና እንዲሰጥ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
- ለክልሉ አመራሮች የተሰጡ ስልጠናዎች ውጤታማነት ግምገማና ጥናት በማድረግ ግኝቶች አደራጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያደርጋል፣ ግኝቶችን ለቀጣይ ስልጠናዎች በግብዓትነት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይሰራል፤
- በክልል ደረጃ ያለውን የፓርቲውን የማሰልጠኛ ማዕከል በበላይነት ይከታተላል፤ ይደግፋል፣
- በክልሉ የሚከናወኑ የፓርቲውን የአቅም ግንባታ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት እየገመገመ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤ የበታች መዋቅሮች ወቅታዊ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ማድረጋቸውንና ሪፖርት ማቅረባቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
- በዘርፉ ተመድበው የሚሰሩ ባለሙያ እና ሰራተኞች የአፈጻጸም ግምገማ በተቀመጠው ጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት መካሄዱን እንዲሁም ሰራተኞች ለስራው በሚያስፈልገው ደረጃ አቅማቸው እንዲገነባ የድጋፍና ክትትል ሥራ ይሰራል፤
- በሥሩ ያሉትን ባለሙያዎችን ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- የሥራ ሪፖርት ለዘርፉ ያቀርባል፤
- ከዘርፍ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣