Skip to main content

 

                                                                አቶ አብርሀም ማርሻሎ                      

                                                                 የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ መልዕክት

ፓርቲያችን ብልፅግና በሀገራችን ባለፉት አምስት አመታት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ መስኮች በርካታ አዎንታዊ ለውጦችን ለማስመዝገብ የቻለ ፓርቲ ነው። 

እነዚህን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች አስጠብቆ ለማስፋት፣ ያለፉ ስህተቶችን ደግሞ ለማረም እንዲሁም የዛሬውንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት በዘላቂነት ለማሟላትና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የሚሰራ ፓርቲ ነው። 

የብልፅግና ዓላማ ወጥነት ያለው ህብረ-ብሔራዊ ውህድ ፓርቲ በመሆን ሰፊውን የሀገራችንን የህዝብ ክፍል የሚያቅፉ ነገር ግን በዕይታ ግድፈት ከሀገራዊ የፖለቲካ ውሳኔ የተገለሉትን ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት የሚሳተፉበትን ፓርቲያዊ አወቃቀር ለማምጣት ማስቻል ሲሆን እውነተኛ ህብረ-ብሔራዊ የሆነው ውህድ ፓርቲያችን የአላማና የተግባር ውህደት በማምጣትና የተሻለ ኃይል በማሰባሰብ በቀጣይ ለላቀ የዓላማ አንድነትና ሀገራዊ ድል የሚያበቃ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ አቅጣጫ የሚከተል ፓርቲ ነው። 

የፓርቲው ጥቅል ዓላማ “የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” ሲሆን የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና ማህበራዊ ገጽታ ያለው የኢኮኖሚ ብልጽግና፣ የህዝቦች መሰረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት ፈጣን እና ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብና ዓለም-አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና የህዝቦችን ድህነትና ኋላ-ቀርነትን ለመቅረፍ መቻልን ያካተተ ነው።  

ፓርቲያችን የግለሰብና የቡድን መብት ተነጣጥለው ሊሄዱ እንደማይችሉ ይገነዘባል። የግለሰብ መብትን በተሟላ መልክ ለማክበር ለቡድን መብቶችም እኩል ዕውቅና እና ትኩረት መስጠት እንደሚገባ፣ እንዲሁም የቡድን መብቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲከበሩ ለማድረግ የግለሰብ መብቶችን ማክበር አስፈላጊ እንደሆነ ፓርቲያችን ያምናል። 

ይህን እውን ለማድረግም ፓርቲያችን እውነተኛ፣ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ ስርዓት ለማጠናከር በጽኑ ይታገላል። ብልጽግናን ማረጋገጥ እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውጥን ያለ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ሙያዊ ብቃት ያዳበሩ ተቋማት እውን ሊሆን እንደማይችል ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል።

 ስለሆነም የዴሞክራሲ ግንባታ ስራዎቻችን ለተቋማት ግንባታና አሰራር ቅድሚያ የሚሰጡና በዚያ ዙሪያ የሚያተኩሩ ይሆናሉ። ስለዚህም ፓርቲያችን የህዝብ አስተዳደር፣ የዴሞክራሲ፣ የሰላም እና የደህንነት እንዲሁም የህግ አስከባሪና የፍትህ ተቋማት እንደየ ባህሪያቸው ነፃ፣ ገለልተኛ እና ብቃት ያላቸው እንዲሆኑ በትጋት ይሰራል። 

የመንግስትና የፖርቲ አሰራሮች በሀገራችን የመደበላለቅ መሰረታዊ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ፓርቲያችን ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል። ከኢኮኖሚ ፕሮግራም አንፃር የቆዩ ኢኮኖሚያዊ ስህተቶችን ያለማወላወል በማረም  አሁን ሀገራችን በደረሰችበት የዕድገት ደረጃ ከዚህ በፊት በተከተልነው የልማት ፋይናንስ ሞዴል በኢኮኖሚና ማህበራዊ መስክ ያስመዘገብነውን ዕድገትና ልማት በተመሳሳይ መንገድ አስጠብቆ ማስቀጠል ከባድ ፈተና የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። 

ያስመዘገብነውን የኢኮኖሚ ዕድገቱን አንድም የዕድገት ምንጮችን በማስፋት፣ በሌላ በኩል ደግሞ በመንግስት ጉድለት ምክንያት የተፈጠረውን የሀገር ሀብት ብክነትና ዝርፊያ በመከላከል፣ የሀገራችንን ህዝቦች ፍትሃዊና የላቀ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው። 

ብልፅግና የኢኮኖሚ ፕሮግራሙ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ መዋቅር (Progressive Capital) በመገንባት በአንድ ክፍለ ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የተመሰረተ የኢኮኖሚ መዋቅር ዘላቂ ዕድገትንም ሆነ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እንደማያረጋግጥ ፓርቲያችን ስለሚያምን ሀገራችን ያላትን አንፃራዊ ዕምቅ አቅሞቿን ታሳቢ በማድርግ ከግብርና በተጨማሪ የኢንዱስትሪ እና ተዛማጅ የአገልግሎት ዘርፎችን በማሳደግ ኢኮኖሚያችን በብዝሃ ዘርፍ የተዋቀረና ዘላቂ ዕድገት ያለው እንዲሆን የሚሰራ ፓርቲ በመሆኑ ይህን ለማሳካት ሀገራችን በዕምቅ ፀጋ የታደለችባቸው ክፍለ ኢኮኖሚዎችን በሙሉ አቅም አሟጦ ወደ ልማት የማስገባት የኢኮኖሚ አቅጣጫን ይከተላል። 

ፓርቲያችን በተለያዩ ሀገራትና ዓለም ክፍሎች ከሚፈጠሩ የኢኮኖሚ ቀውሶች የሚመጡ ጫናዎችን የሚቋቋም የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዲሁም የኢኮኖሚ ነፃነት ያለው ሀገራዊ ኢኮኖሚ ለመገንባት ይሰራል። ይህንንም ለማድረግ ፓርቲያችን ሀገራዊ ፍላጎት እና አቅርቦትን ለማጣጣም ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።