የሀብት አስተዳደር ዘርፍ፣
• የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ተጠሪነቱ ለቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ሆኖ በስሩ አንድ ዳይሬክቶሬት ያለው ሲሆን የሚከተሉት ተግባራትና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-
• የዘርፉን እቅዶች በጀትና የአፈፃፀም ሪፖርቶች በየወቅቱ እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ በትክክል መዘጋጀታቸውን በማረጋገጥ እንዲፀድቅ ያደርጋል፣ ሲፀድቅ ለሚመለከታቸው አካላት ይልካል፣ ሥራውን ያስተባብራል፣ ይገመግማል ይመራል ሪፖርት ያደርጋል • ግብረ መልስ ይሰጣል።
• በዘርፉ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ላይ ከተለያዩ አካላት የሚሰጡ ግብረ መልሶች በዕቅድ ተካተው ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ ስለ ግብረ መልስ አቀባበል ለሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ይላካል፤
• የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን የሰው ሀብት አስተዳደር ሥራዎች የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን መመሪያዎች ተከትለው መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣ በሚታዩ ክፍተቶች ላይ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ በወቅቱ እንዲወሰዱ ያደርጋል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባል፤
• የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን በጀት ለታቀደለት ዓላማ ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ በሥራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣ የበጀት አጠቃቀም ሪፖርት፣ የሂሳብ ትንተና የባንክ ማስታረቅ ሥራዎችና የሂሳብ መግለጫዎች በየወቅቱ መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፣
• የፋይናንስ ህግ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፣ የንብረትና የሀብት አያያዝ ሥርዓት ይዘረጋል፣ የወጪ ቅነሳና የገቢ ማሳደጊያ ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
• የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን ንብረቶች በመንግስት ህጎች መሰረት መተዳደራቸውን ያረጋግጣል፣ በየመጋዘኖችና በተለያዩ ቦታዎች ተከማችተው ያሉ ንብረቶች ተለይተው በህግ መሰረት መወገድ ያለባቸው እንዲወገዱ ያደርጋል፣ ጥቅም ላይ መዋል የሚገባቸው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል።
• የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን የጠቅላላ አገልግሎት ሥራዎች፣ የተሽከርካሪዎች ስምሪትና አስተዳደር፣ የነዳጅና ቅባት አጠቃቀም የመንግስት ህግና ደንብን ተከትሎ መፈፀሙን ያረጋግጣል፣ ችግሮች ሲከሰቱ እንዲፈቱ ያደርጋል።
• በስሩ ያሉትን ዳይሬክቶሬቶች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ይገመግማል፤ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ግብረ-መልስ ይሰጣል፤ሪፖርት ያቀርባል፣
• ከቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣