የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ
የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል።
ከዋና ጽ/ቤቱ ጋር የተናበበ እና ብቃት ያለው የፓርቲ የሚዲያ እና የኮሚዩኒኬሽን ሥርዓትን እስከ ወረዳ በመዘርጋት ለህብረተሰቡ የተሟላ መረጃ እንዲደርስና የጋራ አቋም እንዲያዝበት ያደርጋል፣
የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም በክልሉ የወንድማማችነት/እህትማማችነት እሴትና ህብረ ብሔራዊ አንድነት ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ የትርክትና የመረጃ የበላይነት እንዲይዝ የሚያስችሉ የህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ያከናውናል፣
የፓርቲው እሳቤዎችና ያስመዘገባቸው አገራዊና ክልላዊ ስኬቶች በህዝቡ ልብ ውስጥ እንዲሰርጽ ማድረግ የሚያስችል ዕቅድ አውጥቶ ተፈጻሚ እንዲሆን ማስቻል፤ ይህንንም በቂ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ማድረግ፣
የፓርቲውን ፕሮግራሞች፣ መተዳደሪያ ደንቦች እና እሴቶች ህዝቡ በአግባቡ እንዲያውቃቸው ማድረግ የሚችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋትና ተፈጻሚ እንዲሆኑ መከታተል፤
የፓርቲውንና የመንግስት የለውጥ ስራዎችን ማዕከል ያደረገ ዕቅድ በማዘጋጀት እስከ ታች ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ ማስቀመጥ እና መከታተል፤
በፓርቲው ቁርጠኝነት እና ክትትል በክልሉ የተሰሩ ዋና ዋና ክልላዊ ፕሮጀክቶች ማጉላት የሚያስችል ዕቅድ በማዘጋጀት፣ አጀንዳ የመትከልና ፍሬሚንግ ስልት መከተል፣
የፓርቲውን መልካም ገጽታ ይገነባል፤ የፓርቲዉን መልካም ስም የሚያጠለሹ ጉዳዮችን በመከታተል ይመክታል፣
በዘርፉ መዋቅሩ ውስጥ ያለውን አመራር እና ባለሙያ አቅም መገንባት የሚያስችል ዕቅድ ማዘጋጀትና ተግባራዊ ያደርጋል፤
የፓርቲው የፖለቲካና የአደረጃጀት ሥራዎችና ውሳኔዎች በተለያዩ የብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች ሽፋን እንዲያገኙ ያደርጋል፤
ፓርቲው በሚያዘጋጃቸው ስልጠናዎች፣ ኮንፈረንሶችና መሰል ውይይቶች ለሚዲያዎች መግለጫዎችና ፕሬስ ኮንፈረንሶችን ማዘጋጀትና መስጠት፣
የአመራሩን የፓርቲ የውስጥ ኮሚዩኒኬሽንን ማጠናከር የሚያስችል ስልት ይነድፋል፤ ተግባራዊም ያደርጋል፤
ለአመራሩና ለአባሉ በቀውስ ኮሚዩኒኬሽን ላይ ግልፅነት መፍጠርና ተልዕኮ መስጠት፣
ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር በመተባበር ስለፓርቲው ወቅታዊ መረጃዎችን ይሰጣል፣
የፓርቲውን የፖለቲካና ድርጅት ስራዎችን በተለያዩ ዘዴዎች በቀጣይነት የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል፣
- ከቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣