Skip to main content

                                  የወጣቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል።

  •   በክልሉ ወይም በከተማ መስተዳድሩ በወጣቶች ማብቃትና ተሳትፎ ዙሪያ ወጣቶችን ያማከለ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በማከናወን ወጣቶች እምቅ አቅምና ችሎታቸውን አውጥተው በመጠቀም በሁሉም መስኮች ተሳታፊ፣ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ በትኩረት መስራት፣
  •   ወጣቶችን በአመራርና በውሳኔ ሰጪነት ሚና በህግ አውጪና በህግ ተርጓሚ የሚኖራቸው ስፍራ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል። 
  •  በሀገራችን በሚደረገው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴና መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ለማስፈን በሚደረገው ትግል ወጣቶች ንቁና የተደራጀ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ በውጤት መገንባት፣ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነትን ማጎልበት፣ 
  •  የወጣቶችን ጥቅም የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ሕጐችና ደንቦች፣ ኘሮግራሞች፣ ዕቅዶችና ኘሮጀክቶች በሚወጠኑበት፣ በሚዘጋጁበትና ሥራ ላይ በሚውሉበት ጊዜ ሴቶች የተሳተፋባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ ተግባራዊነታቸውንም መከታተል፣ 
  •  በወጣቶች ዘንድ በእድገት ተኮር ዘርፎች በመሰማራት ረገድ የሚታዩ የአመለካከት ማነቆዎችን በመፍታት በስፋት በተደራጀ መንገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን፤
  •   ስራ አጥ የሆኑ አባላትና አባል ያልሆኑ ወጣቶችን በማደራጀት የስራ እድል በመፍጠር ወደ ስራ በማስገባት ገቢያቸውን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ የክህሎት ስልጠና፣ የብድር፣ የግብዓት አቅርቦትና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ስራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሰራ የመሪነት ሚና መጫወት፤
  •   የወጣቶች የቁጠባ ባህል በማዳበር እንዲቆጥቡ በማድረግ የቆጠቡትን ቁጠባ ለላቀ ኢንቨስትመንት እንዲውል በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ወደ ህብረት ስራና ወደ ሌሎች የላቀ ጥቅም የሚያስገኙ አሰራሮች ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ፤
  •   ከቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣