የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል።
የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ተጠሪነቱ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል።
በክልሉ የሚገኙ የሲቪል ማህበራት፣ የሙያና የብዙሃን ማህበራት፣ ፌዴሬሽኖች፣ ፎረሞች፣ ሌሎች የምሁራንና የባለሃብት አደረጃጀቶችን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤ ይደግፋል፣
የዘርፉን ስራ ያቅዳል፣ ይመራል፤ ይገመግማል፤ ሪፖርት ያደርጋል እንዲሁም በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በመለየትና በመቀመር የማስፋትና፣ ጉድለቶችን ደግሞ ለማረም የሚያስችሉ ስራዎችን ይሰራል፣
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፓርቲዎችን ሁኔታ ይከታተላል፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በየጊዜው በመለየት ለፖለቲካ ስራ በግብአትነት ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
በክልል ደረጃ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ብልፅግናን ወክሎ በመከራከር፣ በመወያየት እና በመመካከር በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ይነድፋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፣
የፖለቲካ ፓርቲዎች በተግባቦት ዴሞክራሲ ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት መዳበር አዎንታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያግዙ አስቻይ ሁኔታዎች ለመፍጠር ይሠራል፣
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሲቪል ማህበራት ለኢኮኖሚ ዕድገትና ብልጽግና፣ ለማህበራዊ ልማትና ፍትህ፣ ለሲቪል ባህል ግንባታ እና ለዜጋ ዲፕሎማሲ ሚናቸው እንዲያድግ ስልቶችን ይነድፋል፤ ስራ ላይ ያውላል፣
የህዝቡ ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ለሁለንተናዊ ብልጽግና አቅም እንዲሆን ለህብረተሰቡ ቅርብ የሆኑ የሲቪል ማህበራትና አደረጃጀቶችን በመጠቀም ያስተባብራል፤ ይከታተላል ይደግፋል፣
ፓርቲው ከክልሉ ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር ያለውን ህጋዊና ተቋማዊ የስራ ግንኙነት ፓርቲውን በመወከል ያስተባብራል፤
በክልሉ የሚገኙ የብልፅግና ሴቶችና ወጣቶች ሊጎች በፓርቲያችን የአደረጃጀትና አሰራር መመሪያ መሰረት መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፣ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
በሊጎች አማካኝነት በክልሉ የሚገኙ የሴቶችና የወጣት አደረጃጀቶችን በማንቀሳቀስ ተሳትፏቸውን፣ ተወዳዳሪነታቸውንና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ስራዎችን ያስተባብራል ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪል ማህበራት እና ሊጎች ሚናቸውን መወጣት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በመቅረጽና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሰጡና የውይይት መድረኮች እንዲካሄዱ ያስተባብራል፤
በክልሉ የሚንቀሰቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪል ማህበራን እና የሊጎችን ፕሮፋይልና መረጃ ያደራጃል፣ ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት ይዘረጋል፣
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪል ማህበራትን እና ሌሎች ብዙሃን አደረጃጀቶች ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መረጃ ያሰባስባል፣ ይተነትናል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ይሰራል፤
አደረጃጀቶች ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ግብረ መልስ ይሰጣል፤ በተግባር ሂደት የሚገኙ ምርጥ ልምዶች በማደራጀት የሚሰፉበትን ሁኔታ ይፈጥራል፤
ከቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣