Skip to main content

                                       የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ

    የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ተጠሪነቱ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆን የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል። 

  •  የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ • ከፓርቲው ፕሮግራም፣ ስትራቴጂክ እቅድ፣ ከዋና ጽ/ቤትና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እቅድ በመነሳት የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ስራ እቅዶችን ያዘጋጃል፤ መፈፀማቸውንም ያረጋግጣል፤
  •  በክልሉ የሚገኙ የፓርቲው አመራሮችና አባላት የፓርቲውን ራዕይ፣ ዓላማና እቅዶች በብቃት መፈጸም በሚችሉበት ደረጃ ላይ ለማድረስና የፖለቲካና የአመራር ብቃታቸውን ለማላቅ የፓርቲውን የፖለቲካ እሳቤዎችና እቅዶች ስርጸት (indoctrination) ሥራ ያከናውናል፣ ያስተባብራል፤     

  • የፓርቲውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የውጭ ግንኙነት ፕሮግራሞች፣ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና እቅዶች በፓርቲው አመራሮችና አባላት ዘንድ እንዲሰርጹ ያደርጋል፤       
     

     የፓርቲው ልሳን ዋነኛ የግንባታ መሳሪያ እንዲሆን፣ በማእከል የሚዘጋጁ ሰነዶች በክልሉ ለሚገኙ አመራሮችና አባላት

  • እንዲደርሱና እንዲፈፀሙ የስልጠናና የውይይት ሠነዶችንና የማስፈፀሚያ እቅዶችን ያዘጋጃል፣ ጠንካራ የሪፖርት፣ የክትትል፣ የድጋፍ እና ግብረ-መልስ ሂደትን በመዘርጋት ይከታተላል፤ ይመራል፣ 

  •  የአመራርና የአባላትን የፖለቲካና የመፈፀም አቅም ለመገንባት የሚረዱ፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር የሚያስችሉና የክልሉን ሁኔታ ያገናዘቡ ወቅታዊ የፖለቲካ ሰነዶችን በማዘጋጀት ለአመራሩና ለአባላት ግንባታ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤ 

  •  በየጊዜው ከነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት ህዝቡን ማንቃትና ማነቃነቅ የሚያስችሉ ሠነዶች ያዘጋጀል፣ የህዝብ ምክክርና ንቅናቄ መድረኮች መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤ ትግበራውንም በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፣ 

  •  ፓርቲው በፕሮግራሙ፣ በማኒፌስቶው፣ በፓርቲው የበላይ አካል የሚተላለፉ የሀገር ውስጥ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ ማህበራዊ ጉዳዮች፣ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ባህል ሥርዓት ግንባታ፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች፣ ወዘተ አቅጣጫዎች በተገቢው የፖለቲካ ቅኝት መፈፀማቸውን ይከታተላል፤

  •   ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት ወቅታዊ የሆኑ ክልላዊ የፖለቲካ ሁኔታዎች በጥልቅ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ሁኔታውን በመገምገም፣ ትንታኔ በመስራት፣ ግኝቱን ለበላይ አካል ያቀርባል፤

  •   የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም በየጊዜው ወቅቱን ጠብቆ የህዝብ አስተያየቶች ማሰባሰብና፤ መተንተን፤ ስለ ቀጣይ የፖለቲካ- ኢኮኖሚ አዝማሚያዎች ሁኔታ የቢሆን ትንቢያዎች (scenarios) ማመላከት፤ ለሚመለተከው አካል መረጃ ወይም ግብረ መልስ እንዲደርስ ማድረግ …ወዘተ ሥራዎች በተገቢው መንገድ መፈፀማቸውን ያረጋግጣል፤

  •   ዋና ዋና የሚባሉ ሀገራዊ የፖለቲካል ኢኮኖሚ አጀንዳዎች፤ የአጀንዳዎቹ ተዋናዮችና የኃይል አሰላለፍ ሚዛን በመለየት የፓርቲ የበላይነት ለመያዝ የሚያስችሉ ሥራዎችን አቅዶ አፈፃፀሙን ያስተባብራል፣ 

  •  የፓርቲው አመራር ሰጪነት፣ ህዝብ የማስተዳደርና ሀገርን የመምራት ቁመናውና የፓርቲው ህዝባዊ ቅቡልነት (legitimacy) ያለበትን ደረጃ ለመረዳት ከሚመለከታቸው ዘርፎች ጋር በመተባበር የህዝብ አስተያየት ዳሰሳ ጥናት (public opinion survey) መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤

  •   በየጊዜው የሚመዘገቡ ድሎችና ስኬቶችን መለየትና መቀመር፣ የቀደመውን ትሩፋትና ስኬት በማስጠበቅና በማጠናከር በቀደመው የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ድልም ሽንፈትም እንደነበረ በመገንዘብ በጎውን በማስቀጠልና በማሳደግ፣ ክፉውን ማረምና አለመድገም የሚያስችሉ ፓርቲያችን በክልሉ የፖለቲካ ትርክት የበላይነት እንዲይዝ ይሠራል፤

  •   የብሔሮችን መብት የግለሰብ መብቶች ሚዛኑ ለመጠበቅ የሚረዱ፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነትን እሴት ለመገንባት የሚያግዙ፣ ማህበራዊ ትስስራችንን የሚያጠናክሩ፣ በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ለመፍጠር የሚጠቅሙ፣ ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል እንዲሁም ለሁሉም ዜጎቿ የምትመች፣ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ያቀፈችና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠች፤ የበለፀገችና ጠንካራ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችሉ የፖለቲካ ሥራዎች በክልሉ በአግባቡ እንዲሰሩ ይመራል፤ ያስተባብራል፣

  •   ከየመድረኩ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚዛመዱ ወቅታዊ እና የጋራ አመለካከት ለመፍጠር የሚያግዙ መልዕክቶችንና አጀንዳዎችን በመቅረፅ አመራርና አባላት የተሟላ ግልፅነት እንዲኖራቸው ያደርጋል፣ 

  •  በክልሉ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ሰላማቸው ተጠብቆ ብቁ ዜጋ ማፍራት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲጠናከር ለማድረግ እንዲሁም በተቋማቱ የሚካሄዱ የፖለቲካ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በበላይነት ይመራል፤ ያቀናጃል፤ ያስተባብራል፣

  •   በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ምሁራን ለሀገር ግንባታ ዓላማዎች ስኬታማነት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ግንዛቤና ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤

  •   መሰረታዊ ድርጅቶችና ህዋሳት በወሳኝ አጀንዳዎች ላይ ለፓርቲውና ለአባላቱ እሴት በሚጨምር መልኩ እንዲወያዩና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል የድጋፍና ክትትል ሥራ መሰራቱን ያረጋግጣል፣

  •   የሚካሄዱ ሀገራዊና አከባቢያዊ ምርጫዎችን በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያስችል እቅዶችና የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በመቅረጽና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር መፈፀማቸውን ያረጋግጣል፤

  •   የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ የአመራራችንና የአባላት ስልጠና ፍላጎት ይለያል፣ ለሚመለከታቸው አካላት አደራጅቶ ያቀርባል፤

  •   ፍላጎታቸውን መሰረት በማድረግ ለክልሉ አመራሮችና አባላት ውጤታማ ስልጠና እንዲሰጥ ያስተባብራል፣

  •   ለክልሉ አመራሮች የተሰጡ ስልጠናዎች ውጤታማነት ግምገማና ጥናት በማድረግ ግኝቶችን አደራጅቶ ለሚመለከታው አካላት ሪፖርት ያደርጋል፣ ግኝቶችን ለቀጣይ ስልጠናዎች በግብዓትነት ይጠቀማል፤

  •   በክልል ደረጃ ያለውን የፓርቲውን የማሰልጠኛ ማዕከል በበላይነት ይከታተላል፤ ይደግፋል፣

  •   የፓርቲውን የፖለቲካ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት እየገመገመ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤ የበታች መዋቅሮች ወቅታዊ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ማድረጋቸውንና ሪፖርት ማቅረባቸውን ያረጋግጣል፣ 

  •  ለዘርፉ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስፈልገው የፋይናንስ፣ የማቴሪያል እንዲሁም የሰው ኃይል በብዛት እና በጥራት (ክህሎት እና ዕውቀት) መሟላቱን ያረጋግጣል፤

  •   በዘርፉ ተመድበው የሚሰሩ ባለሙያ እና ሰራተኞች የአፈጻጸም ግምገማ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት መካሄዱን እንዲሁም ሰራተኞች ለስራው በሚያስፈልገው ደረጃ አቅማቸው መገንባቱን ያረጋግጣል፤

  •   በክልሉ የሚገኙ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች (በመንግስት የስራ ኃላፊነት ላይ ያሉትን ጨምሮ) በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ያማክራል፤ ይደግፋል፣ 

  • ከቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣