አቶ  አብርሃም  ማርሻሎ 

                                           የሲዳማ ክልል ብልጽና ፓርቲ ቅ/ጽ ቤት ኃላፊ                                         

ፓርቲያችን ብልፅግና በሀገራችን ባለፉት አምስት አመታት በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ መስኮች በርካታ አዎንታዊ ለውጦችን ለማስመዝገብ የቻለ ፓርቲ ነው። እነዚህን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦች አስጠብቆ ለማስፋት፣ ያለፉ ስህተቶችን ደግሞ ለማረም እንዲሁም የዛሬውንና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት በዘላቂነት ለማሟላትና ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር የሚሰራ ፓርቲ ነው።

የብልፅግና ዓላማ ወጥነት ያለው ህብረ-ብሔራዊ ውህድ ፓርቲ በመሆን ሰፊውን የሀገራችንን የህዝብ ክፍል የሚያቅፉ ነገር ግን በዕይታ ግድፈት ከሀገራዊ የፖለቲካ ውሳኔ የተገለሉትን ኢትዮጵያዊያን በእኩልነት የሚሳተፉበትን ፓርቲያዊ አወቃቀር ለማምጣት ማስቻል ሲሆን እውነተኛ ህብረ-ብሔራዊ የሆነው ውህድ ፓርቲያችን የአላማና የተግባር ውህደት በማምጣትና የተሻለ ኃይል በማሰባሰብ በቀጣይ ለላቀ የዓላማ አንድነትና ሀገራዊ ድል የሚያበቃ እንዲሁም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ አቅጣጫ የሚከተል ፓርቲ ነው።

የፓርቲው ጥቅል ዓላማ “የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” ሲሆን የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና ማህበራዊ ገጽታ ያለው የኢኮኖሚ ብልጽግና፣ የህዝቦች መሰረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት ፈጣን እና ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብና ዓለም-አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና የህዝቦችን ድህነትና ኋላ-ቀርነትን ለመቅረፍ መቻልን ያካተተ ነው።  

ፓርቲያችን የግለሰብና የቡድን መብት ተነጣጥለው ሊሄዱ እንደማይችሉ ይገነዘባል። የግለሰብ መብትን በተሟላ መልክ ለማክበር ለቡድን መብቶችም እኩል ዕውቅና እና ትኩረት መስጠት እንደሚገባ፣ እንዲሁም የቡድን መብቶች በተሟላ ሁኔታ እንዲከበሩ ለማድረግ የግለሰብ መብቶችን ማክበር አስፈላጊ እንደሆነ ፓርቲያችን ያምናል። ይህን እውን ለማድረግም ፓርቲያችን እውነተኛ፣ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ ስርዓት ለማጠናከር በጽኑ ይታገላል።

Read more

ወቅታዊ ዜናዎች

Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Loosu Dandootenna Interprayizootu latishshi

  

የፓርቲያችን ጥቅል ዓላማ  

ብልጽግና ስንል ፈርጀ ብዙ ትርጓሜን አዝሎ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ እና ማህበራዊ ገጽታ ያለው ነው። የኢኮኖሚ ብልጽግና፣ የህዝቦች መሰረታዊ ፍላጎቶች በተገቢና በዘላቂነት ለማሟላት ፈጣን እና ሁለንተናዊ ዕድገትን በማስመዝገብና ዓለም-አቀፋዊ ተወዳዳሪነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና የህዝቦችን ድህነትና ኋላ-ቀርነትን ለመቅረፍ መቻልን ያካተተ ነው።

የብልፅግና ራዕይ  

የሚናልመዉ የኢትዮጵያ ብልፅግና ቁሳዊ፤ሰብአዊና እና የማይዳሰሱ ማኅበራዊ ሀብቶቻችንን አቀናጅተን በማነጽ የምንፈጥረዉ አቅም፤ያም አቅም በተራዉ የሚፈጥረዉ ጥሪትና የሚገነባዉ እርካታን የያዘ ሁለመናዊ ብልፅግና ነዉ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ መለያ እሴቶች  

አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መገንባት ነው፡፡ ህብረ ብሔራዊ ስንል የብሔር፣ የሐይማኖት ወይም ሌላ ማንነቶችን ያቀፈና ማንንም ያላገለለ ማህበረሰብ ማለታችን ነው፡፡

 

ፎቶዎች

FEEDBACK