የሲዳማ ክልል መንግስት የህገ-ወጥ ኮንትሮባን ንግድ መከላከልና ኑሮ ውድነት ማሻሻያ የጋራ ግብረ ኃይል የ2016 በጀት ዓመት ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል። የሲዳማ ክልል መንግስት የህገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ መከላከልና ኑሮ ውድነት ማሻሻያ የጋራ ግብረ ኃይል ህገ ወጥ ንግድና የኑሮ ውድነት ድርጊቶችን መከላከል ለጋራ ተጠቃሚነት በሚል መሪ ቃል የ2016 በጀት ዓመት ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ በሀዋሳ ከተማ ላይ እያካሄደ ይገኛል። በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የግብሬ-ኃይሉ ሰብሳቢና የክልሉ ም/ፕሬዝደንትና የትም/ት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ እንደገለፁት መንግስትና መንግስትን የሚመራው ፓርቲያችን ብልፅግና ፍትሃዊ የንግድ ስርዓትን በመዘርጋት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን በመቆጣጠርና በመግታት በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድ ስርዓትን በመትከል ሀገራዊ የብልፅግና ራዕይ ለማሳካት ብርቱ ትግል እያደረገ እንደሚገኝ አውስተው በክልሉ የተጀመረውም የህገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ንግድ መከላከልና ኑሮ ውድነት ማሻሻያ