Skip to main content

                                                       የፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ  የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል።

  • የፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ተጠሪነቱ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆን በስሩ አንድ ምክትል የዘርፍ ኃላፊና ሁለት ዳይሬክቶሬቶች ይኖሩታል። 
  • የዘርፉ ኃላፊና በስሩ ያሉ አካላት ተግባርና ኃላፊነትም ከዚህ የሚከተለው ይሆናል። ሀ. የፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ 
  •  ከፓርቲው ፕሮግራም፣ ስትራቴጂክ እቅድ፣ ከዋና ጽ/ቤትና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እቅድ በመነሳት የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የአደረጃጀት ስራ እቅዶችን ያዘጋጃል፤ መፈፀማቸውን ያረጋግጣል፤ 
  •  በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አደረጃጀቶች በአደረጃጀትና አሰራር መመሪያው መሰረት መደራጀታቸውን፣በግንባር ቀደሞች መመራታቸውን፣ ተሳስረው የሚንቀሳቀሱበት አግባብ መፈጠሩን፣ እያንዳንዱ አደረጃጀትና መዋቅር በደረጃው ባለው ተልዕኮና አሠራር ላይ ግልጽ ሆኖና እቅድ ኖሮት ወደ ተግባር መሰማራቱንና ለፓርቲው አቅም ሆነው ማገልገላቸውን ያረጋግጣል፤ 
  •  በመተዳደሪያ ደንብና ተያያዥነት ባላቸው የፓርቲው አሰራር ስርዓቶች መሰረት የአባላት ምልመላ ሥራዎች በጥራት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤ 
  •  የብልጽግና መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች በፓርቲው የወጡት የአደረጃጀትና የአሰራር መመሪያዎች በሁሉም አባላትና አመራር አካላት ታውቀው፣ ታምኖባቸውና በተሟላ መልኩ ተግባር ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል። ከመመሪያ እና ከአሰራር ውጪ የሚሄዱ አባላትን በፓርቲው ህግና ደንብ መሰረት ተገቢው የእርምት እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን ያረጋግጣል፤  በየደረጃው ያሉ የአደረጃጀት መዋቅሮች ከማዕከላዊ ኮሚቴውና በየደረጃው ካሉ የፓርቲ ጽ/ቤቶች ዕቅድ ተነስተው ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀታቸውን እና አፈጻጸማቸውንም ያረጋግጣል፣
  •   የፓርቲውን የአደረጃጀት ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት እየገመገመ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፣ የበታች መዋቅሮች ወቅታዊ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ማድረጋቸውንና ሪፖርት ማቅረባቸውን ያረጋግጣል፤ 
  •  በፓርቲው የውስጥ ምርጫ ስርዓት መሰረት በየደረጃው ምርጫዎች መካሄዳቸውን ያረጋግጣል፣  በየደረጃው ያሉ የፓርቲው መዋቅሮች ለተለያዩ መደቦች ተተኪ አመራሮችና ካድሬዎች መመልመላቸውንና በአመራር ቋት መያዛቸው ያረጋግጣል፤ 
  •  በክፍት የአመራር ቦታዎች ላይ በፓርቲው የምደባ ስርዓት መሰረት እጩዎች መለየታቸውን፣ በተገቢው ሂደት መተላለፉንና ምደባ መከናወኑን ያረጋግጣል፤ 
  •  በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አመራሮች በምዘና መመሪያው መሰረት መመዘናቸውን ያረጋግጣል፤ 
  •  በክልሉ ከሚገኙ አመራሮች መካከል በብልጽግና እሳቤዎች ዙሪያ ባላቸው የጠራና የጸና ግንዛቤ፣ የብልጽግናን ራእይ እውን ለማድረግ ባላቸው ቁርጠኝነት፣ በብቃታቸው፣ 
  •  በአስተሳሰብ ጥራታቸው፣ በባህሪያቸውና በአፈፃፀም ውጤታቸው የላቁትን አመራሮች መለየታቸውንና በየደረጃው በኮር አመራርነት መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፤ 
  •  የአባላትና የአመራር መረጃዎችና ሰነዶች በአይነት ተለይተው ወቅታዊነታቸውና ደህንነታቸውም ተጠብቆ መደራጀታቸውን፣ እንዲሁም መረጃዎች ለድርጅታዊ ውሳኔዎች መዋላቸውን ያረጋግጣል፣ 
  •  ለዘርፉ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስፈልገው የፋይናንስ እና የማቴሪያል እንዲሁም የሰው ኃይል በብዛት እና በጥራት (ክህሎት እና ዕውቀት) መሟላቱን ያረጋግጣል፤ በዘርፉ ተመድበው የሚሰሩ ባለሙያ ሰራተኞች የአፈጻጸም ግምገማ በተቀመጠው ጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት መካሄዱን እንዲሁም ሰራተኞች ለስራው በሚያስፈልገው ደረጃ አቅማቸው መገንባቱን ያረጋግጣል፤ 
  •  በየአደረጃጀቱ የታቀፉ አባላት በፓርቲው ላይ የሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ቅሬታዎች እንደ ጥያቄዎቹ/ቅሬታዎቹ ተጨባጭነት አስፈላጊው መፍትሄ ወይም ማብራሪያ እየተሰጠባቸው መፈታታቸውንና መግባባት ላይ መደረሱን ያረጋግጣል። 
  • በተለያዩ አደረጃጀቶች መካከል የልምድ ልውውጥ ያከናውናል፤ ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮና አደራጅቶ ረቂቅ ሰነድ ለፖለቲካ ዘርፍ ያቀርባል፤ የፀደቁ ምርጥ ልምዶች (best practices) ማጋሪያ ሰነዶች ለሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎች እና አደረጃጀቶች መድረሳቸውንና ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል። 
  •  ከቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣ የአደረጃጀት ዳይሬክቶሬት 
  •  የዘርፉን እቅድ መነሻ በማድረግ የአደረጃጀት ስራ እቅዶችን ያዘጋጃል፣ ዝርዝር መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ይፈጽማል፤ ያስፈፅማል፣ 
  •  በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አደረጃጀቶች በአደረጃጀትና አሰራር መመሪያው መሰረት መደራጀታቸውን፣ በግንባር ቀደሞች መመራታቸውን፣ ተሳስረው የሚንቀሳቀሱበት አግባብ መፈጠሩን፣ እያንዳንዱ አደረጃጀትና መዋቅር በየደረጃው ባለው ተልዕኮና አሠራር ላይ ግልጽ ሆኖ እና እቅድ ኖሮት ወደ ተግባር መሰማራቱንና ለፓርቲው አቅም ሆነው ማገልገላቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ 
  •  በመተዳደሪያ ደንብና ተያያዥነት ባላቸው የፓርቲው አሰራር ስርዓቶች መሰረት የአባላት ምልመላ ሥራዎች በጥራት መከናወናቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
  •   የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች በፓርቲው የወጡት የአደረጃጀትና የአሰራር መመሪያዎች በሁሉም አባላትና አመራር አካላት ታውቀው፣ ታምኖባቸውና በተሟላ መልኩ ተግባር ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል። ከመመሪያ እና ከአሰራር ውጪ የሚሄዱ አባላትን በፓርቲው ህግና ደንብ መሰረት ተገቢው የእርምት እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
  •   በየደረጃው ያሉ የአደረጃጀት መዋቅሮች ከማዕከላዊ ኮሚቴውና በየደረጃው ካሉ የፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ዕቅድ ተነስተው ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤ የእቅድ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤ • የፓርቲውን የአደረጃጀት ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት እየገመገመ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤ የበታች መዋቅሮች ወቅታዊ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ማድረጋቸውንና ሪፖርት ማቅረባቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
  •   በፓርቲው የውስጥ ምርጫ ስርዓት መሰረት በየደረጃው ምርጫዎች መካሄዳቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ • በየደረጃው ያሉ የፓርቲው መዋቅሮች ለተለያዩ መደቦች ተተኪ አመራሮችና ካድሬዎች መመልመላቸውንና በአመራር ቋት መያዛቸው ይከታተላል፤
  •  ይደግፋል፤
  •   በክፍት የአመራር ቦታዎች ላይ በፓርቲው የምደባ ስርዓት መሰረት እጩዎች 
  •  መለየታቸውን፣ በተገቢው ሂደት መታለፉንና ምደባ መከናወኑን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
  •   በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አመራሮች በምዘና መመሪያው መሰረት መመዘናቸውን
  •   ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ 
  •  በክልሉ ከሚገኙ አመራሮች መካከል በብልጽግና እሳቤዎች ዙሪያ ባላቸው የጠራና የጸና
  •   ግንዛቤ፣ የብልጽግናን ራእይ እውን ለማድረግ ባላቸው ቁርጠኝነት፣ በብቃታቸው፣
  •   በአስተሳሰብ ጥራታቸው፣ በባህሪያቸውና በአፈፃፀም ውጤታቸው የላቁትን አመራሮች 
  •  መለየታቸውንና በየደረጃው በኮር አመራርነት መደራጀታቸውን ይከታተላል፤
  •   ይደግፋል፤ 
  •  የአባላትና የአመራር መረጃዎችና ሰነዶች በአይነት ተለይተው ወቅታዊነታቸውና 
  •  ደህንነታቸውም ተጠብቆ መደራጅታቸውን እንዲሁም መረጃዎች ለድርጅታዊ ውሳኔዎች 
  •  መዋላቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
  •   ለዘርፉ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስፈልገው የፋይናንስ እና የማቴሪያል እንዲሁም የሰው ኃይል በብዛት እና በጥራት (ክህሎት እና ዕውቀት) መሟላቱን ያረጋግጣል፤ በዘርፉ ተመድበው የሚሰሩ ባለሙያ ሰራተኞች የአፈጻጸም ግምገማ በተቀመጠው ጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት መካሄዱን እንዲሁም ሰራተኞች ለስራው በሚያስፈልገው ደረጃ አቅማቸው መገንባቱን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
  •   በየአደረጃጀቱ የታቀፉ አባላት በፓርቲው ላይ የሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ቅሬታዎች እንደ ጥያቄዎቹ/ቅሬታዎቹ ተጨባጭነት አስፈላጊው መፍትሄ ወይም ማብራሪያ እየተሰጠባቸው መፈታታቸውንና መግባባት ላይ መደረሱን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
  •   በተለያዩ አደረጃጀቶች መካከል የልምድ ልውውጥ ያከናውናል፤ ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮና አደራጅቶ ረቂቅ ሰነድ ለዘርፉ ያቀርባል፤ የፀደቁ ምርጥ ልምዶች (best practices) ማጋሪያ ሰነዶች ለሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎች እና አደረጃጀቶች
  •   መድረሳቸውንና ውጤታማ መሆናቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ • በሥሩ ያሉትን ባለሙያዎችን ይመራል፤ ያስተባብራል፤
  •   የሥራ ሪፖርት ለዘርፉ ያቀርባል፤
  •   ከዘርፉ ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣
  •   የ ክልል ተቋማት ክትትል ዳይሬክቶሬት
  •   በክልል ደረጃ ባሉ ተቋማት ውስጥ ያሉ የፓርቲ አባላትና አመራሮች የአደረጃጀት፣ የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በበላይነት ያስተባብራል
  •   በክልል ተቋማት ያሉ የፓርቲ አደረጃጀቶች የፓርቲውን አላማ አንዲያስፈጽሙ ይከታተላል፣ ያግዛል እንዲሁም ያጠናክራል።
  •   የፓርቲ አደረጃጀቶች ውስጣዊ አሰራር ዴሞክራሲያዊ እና አሳታፊ መሆኑን ይከታተላል፤ አስፈላጊውን ድጋፍም ያደርጋል፤
  •   በክልል ተቋማት ውስጥ ከሚሰሩ ሠራተኞች የአባላት ምልመላ ሥራ በአሰራሩ መሰረት የሚፈፀም መሆኑን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣
  •   በክልል ተቋማት ካሉ አባላትና አመራር ተተኪ አመራሮችና ካድሬዎች ይመለምላል፣ ክፍት የአመራር ቦታዎችን በወቅቱ በመለየት በአሰራሩ መሰረት እንዲተኩ ለዘርፉ ኃላፊ ሪፖርት ያደርጋል፤
  •   አባላትና አመራሮች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት የፓርቲውን ዓላማ እያስፈጸሙ መሆናቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
  •   በየአደረጃጀቱ የሚደረጉ የአባላት ውይይቶች በመመሪያና አሰራሮች መሰረት በትክክል መካሄዳቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
  •   በክልል ተቋማት ውስጥ ያሉ አደረጃጀቶች፣ አመራሮችና አባላት የአፈፃፀም ግምገማዎችን በመደበኛነት ያቅዳል፣ ግምገማዎች በተቀመጠላቸው ጊዜና መርሃ-ግብር መሰረት በትክክል መካሄዳቸውን ያረጋግጣል፣ የአባላትና የአመራሮች አፈፃፀም እየተለዩና ደረጃ እየተሰጣቸው፣ የአፈፃፀም ችግሮችም ተለይተው በዘላቂነት እየተፈቱ፣ አፈፃፀሞቹም እየተሻሻሉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣
  •   በሥሩ ያሉትን ባለሙያዎችን ይመራል፤ ያስተባብራል፤
  •   የሥራ ሪፖርት ለዘርፉ ያቀርባል፤
  •   ከዘርፍ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣