Skip to main content
image news

ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብረሃም ማርሻሎ ገለፁ ።

ይህ የተገለጸው የሲዳማ ክልል የሥራ ፣ክህሎት እና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ የ2016 ዓ.ም የንቅናቄ መድረክ ባካሄዱበት ወቅት ነው ።

በንቅናቄው መድረክ ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንደተናገሩት ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው በማለት ለዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚነት ላይ እንደ ክልል ተጨባጭ ለውጥ ለማስመዝገብ ቅንጅታዊ አሰራሮች መጠናከር እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።