የሴቶች ሊግ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል።
- የክልሉ ወይም የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች እኩልነትን ለማረጋገጥ ሴቶች በልማት፣ በሰላም፣ በመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ በታታሪነት እንዲሳተፉ ይሰራል፤
- የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለዘለቄታው የሚፈታበትን መሰረት መጣል፣ እንዲሁም ሴቶች በተለያዩ መስኮች ላይ የውሳኔ ሰጭነት ብቃታቸው ማጎልበት የሚያስችል መደላደል መፍጠር እና በውጤቱም ተጠቃሚነታቸው ማረጋገጥ፤
- ሴቶችን ማብቃትና በስርዓተ ፆታ እኩልነት ሴቶች እኩል ዕድል የማግኘት መብታቸውና ከማናቸውም ጥቃትና መድሎ የተጠበቁና በሁሉም መስክ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በሚደረገው ትግል ሴቶች ንቁና የተደራጀ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ በውጤቱም መገንባት እንዲሁም የሴቶችን ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ማጎልበት፣
- ሴቶች በተለያዩ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ፈንዶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን የማረጋገጥና የማስተሳሰር ስራ፤ ሴቶች በብድር፣በህብረት ስራ ማህበራት፣ በገጠር መሬት ባለቤትነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራት፤
- ለሴቶች ተስማሚ የሆኑ ጊዜና ጉልበት ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ከአፍላቂ ተቋማት ጋር በመተባበርና በመቀናጀት የመለየትና ሴቶች በቴክኖሎጂዎቹ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማገዝ ስራ መስራት፣
- ሕብረተሰቡ በሴቶች ላይ እንዲሁም ሴቶች በራሳቸው ላይ ያላቸው የዝቅተኝነትና የበታችነት አመለካከት ተወግዶ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ጤናማ ግንዛቤ መፍጠር፣ ሁኔታዎችንም ማመቻቸትና ማዳበር፣
- የሴቶችን ጥቅም የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ሕጐችና ደንቦች፣ ኘሮግራሞች፣ ዕቅዶችና ኘሮጀክቶች በሚወጠኑበት፣ በሚዘጋጁበትና ሥራ ላይ በሚውሉበት ጊዜ ሴቶች የተሳተፉባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ ተግባራዊነታቸውንም መከታተል፣
- አካል ጉዳተኞች፣ ተጋላጭ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ተጠቃሚ ሆነው አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት ሁኔታ ላይ በአደረጃጀቶቻችን አማካይነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት፤
- አቅመ ደካማዎችንና አረጋውያን ሴቶች ልዩ ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ መፍጠር እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ተጋላጭ ሴቶችን በማህበራዊ በኢኮኖሚያዊና ስነልቦና ድጋፍ እንዲያገኙ ዕድል መፍጠር፤
- ከቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣