Skip to main content

 

                                 የፖለቲካ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል። 

  •  ከፓርቲው ዓላማዎች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመነሳት የተዘጋጀውን የፓርቲውን የፖለቲካ ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት ያደረገ በክልሉ ተፈጻሚ የሚሆን የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የፖለቲካ ስራ እቅዶችን ያዘጋጃል፤ ዝርዝር መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ያስፈፅማል፤

  •   በክልሉ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው የፖለቲካ አደረጃጀቶች ከክልላዊ ዕቅድ ተነስተው ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፣ የእቅድ አፈጻጸማቸውንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤

  •  ከፓርቲው ፕሮግራም፣ ስትራቴጂክ እቅድ፣ ከዋና ጽ/ቤትና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እቅድ በመነሳት የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ስራ እቅዶችን ያዘጋጃል፤ መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣

  •   በክልሉ የሚገኙ የፓርቲው አመራሮችና አባላት የፓርቲውን ራዕይ፣ ዓላማና እቅዶችበብቃት መፈጸም በሚችሉበት ደረጃ ላይ ለማድረስና የፖለቲካና የአመራር ብቃታቸውን ለማላቅ የፓርቲውን ፖለቲካዊ እሳቤዎችና እቅዶች ስርፀት(indoctrination) ሥራ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣

  •   የፓርቲው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊና የውጭ ግንኙነት ፕሮግራሞች፣ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና እቅዶች በፓርቲው አመራሮችና አባላት ዘንድ እንዲሰርጹ ይሰራል፣

  •   የፓርቲው ልሳን ዋነኛ የግንባታ መሳሪያ እንዲሆን፣ በማእከል የሚዘጋጁ ሰነዶች በክልሉ ለሚገኙ አመራሮችና አባላት እንዲደርሱና እንዲፈፀሙ የስልጠናና የውይይት ሠነዶችንና የማስፈፀሚያ እቅዶችን ያዘጋጃል፣ ጠንካራ የሪፖርት፣ የክትትል፣ የድጋፍ እና ግብር-መልስ ሂደትን በመዘርጋት ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ 

  •  የአመራርና አባላትን የፖለቲካና የመፈፀም አቅም ለመገንባት የሚረዱ፣ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር የሚያስችሉና የክልሉን ሁኔታ ያገናዘቡ ወቅታዊ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አደረጃጀትና መዋቅር የፀደቀ የፖለቲካ ሰነዶችን በማዘጋጀት ለአመራሩና ለአባላት ግንባታ ጥቅም ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፤

  •   በየጊዜው ከነባራዊ ሁኔታዎች በመነሳት ህዝቡን ማንቃትና ማነቃነቅ የሚያስችሉ ሠነዶች ያዘጋጀል፤ የህዝብ ምክክርና ንቅናቄ መድረኮች መዘጋጀታቸውን ያረጋግጣል፤ ትግበራውንም በተመለከተ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤

  •   ፓርቲው በፕሮግራሙ፣ በማኒፌስቶው፣ በፓርቲው የበላይ አካል የሚተላለፉ የሀገር ውስጥ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና፣ ማህበራዊ ጉዳዮች፣ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ባህል ሥርዓት ግንባታ፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች፣ ወዘተ አቅጣጫዎች በተገቢው የፖለቲካ ቅኝት መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣

  •   ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት ወቅታዊ የሆኑ ክልላዊ የፖለቲካ ሁኔታዎች በጥልቅ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ሁኔታውን በመገምገም፣ ትንታኔ በመስራት፤ ግኝቱን ለዘርፍ ኃላፊ ያቀርባል

  •   የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም በየጊዜው ወቅቱን ጠብቆ የህዝብ አስተያየቶች ማሰባሰብና፤ መተንተን፤ ስለ ቀጣይ የፖለቲካ- ኢኮኖሚ አዝማሚያዎች ሁኔታ የሚሆን ትንበያዎች (scenarios) ማመላከት፤ ለሚመለተከው አካል መረጃ ወይም ግብረ መልስ እንዲደርስ ማድረግ፤ …ወዘተ ሥራዎች በተገቢው መንገድ መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፤

  •   ዋና ዋና የሚባሉ ሀገራዊ የፖለቲካል ኢኮኖሚ አጀንዳዎች፤ የአጀንዳዎቹ ተዋናዮችና የኃይል አሠላለፍ ሚዛኑን በመለየት ፓርቲው የበላይነት ለመያዝ የሚያስችሉት ሥራዎችን አቅዶ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ ይደግፋል፣

  •   የፓርቲው አመራር ሰጪነትና ህዝብን የማስተዳደርና ሀገርን የመምራት ቁመናውና የፓርቲው ህዝባዊ ቅቡልነት (legitimacy) ያለበት ደረጃ ለመረዳት ከሚመለከታቸው ዘርፎች ጋር በመተባባር የህዝብ አስተያየት ዳሰሳ ጥናት (public opinion survey) መደረጋቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፤

  •   በየጊዜው የሚመዘገቡ ድሎችና ስኬቶችን መለየትና መቀመር፣ የቀደመውን ትሩፋትና ስኬት በማስጠበቅና በማጠናከር በቀደመው የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ ድልም ሽንፈትም እንደነበረ በመገንዘብ በጎውን በማስቀጠልና በማሳደግ፣ ክፉውን ማረምና አለመድገም የሚያስችሉ ፓርቲያችን በክልሉ የፖለቲካ ትርክት የበላይነት እንዲይዝ ይሠራል፤

  •   የብሔሮች እና የግለሰብ መብቶች ሚዛን ለመጠበቅ የሚረዱ፣ የወንድማማችነትና እህትማማችነትን እሴት ለመገንባት የሚያግዙ፣ ማህበራዊ ትስስራችንን የሚያጠናክሩ፣ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አደረጃጀትና መዋቅር የፀደቀ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚጠቅሙ፣ ጠንካራ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመገንባት የሚያስችሉ እንዲሁም ለሁሉም ዜጎቿ የምትመች፣ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያቀፈችና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠች፤ የበለፀገችና ጠንካራ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያስችሉ የፖለቲካ ሥራዎች በክልሉ በአግባቡ እንዲሰሩ ይከታተላል፤ ይደግፋል፣

  •   ወቅታዊ ከየመድረኩ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚዛመዱ እና የጋራ አመለካከት ለመፍጠር የሚያግዙ መልዕክቶችንና አጀንዳዎችን በመቅረፅ አመራርና አባላት የተሟላ ግልፅነት እንዲኖራቸው ያደርጋል።

  •   በክልሉ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ሰላማቸው ተጠብቆ ብቁ ዜጋ ማፍራት የሚችሉበት ሁኔታ እንዲጠናከር ለማድረግና በተቋማቱ የሚካሄዱ የፖለቲካ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣

  •   በትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ምሁራን ለሀገር ግንባታ ዓላማዎች ስኬታማነት የበኩላቸውን እንዲወጡ ግንዛቤና ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤

  •   መሰረታዊ ድርጅቶችና ህዋሳት በወሳኝ አጀንዳዎች ላይ ለፓርቲውና ለአባላቱ እሴት በሚጨምር መልኩ እንዲወያዩና ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል የድጋፍና ክትትል ሥራ መሰራቱን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣

  •   የሚካሄዱ ሀገራዊና አከባቢያዊ ምርጫዎችን በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ እቅዶችና የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን በመቅረጽና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር መፈፀማቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ 

  •  በክልሉ የሚከናወኑ የፓርቲው የፖለቲካ ስራዎች ዕቅድ አፈጻጸም በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት እየገመገመ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤ የበታች መዋቅሮች ወቅታዊ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ማድረጋቸውንና ሪፖርት ማቅረባቸውን ያረጋግጣል።

  •   ለዘርፉ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስፈልገው የፋይናንስ እና የማቴሪያል እንዲሁም የሰው ኃይል በብዛት እና በጥራት (ክህሎት እና ዕውቀት) መሟላቱን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣

  •   በዘርፉ ተመድበው የሚሰሩ ባለሙያ እና ሰራተኞች የአፈጻጸም ግምገማ በተቀመጠው ጊዜ ሰሌዳ እና መስፈርት መሰረት መካሄዱን እንዲሁም ሰራተኞች ለስራው በሚያስፈልገው ደረጃ አቅማቸው እንዲገነባ የድጋፍና ክትትል ሥራ ይሰራል፤

  •   በሥሩ ያሉትን ባለሙያዎችን ይመራል፤ ያስተባብራል፤ የክልል፣ 

  •  የሥራ ሪፖርት ለዘርፉ ያቀርባል፤
  •   ከዘርፍ ኃላፊው የሚሰጡ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፣