Skip to main content
image news

መደመር ማንንም የሚያገልል ማንንም የሚያስገድድ ሂደት አይደለም።

መደመር ማንንም የሚያገልል ማንንም የሚያስገድድ ሂደት አይደለም። እርቅና ሰላምን የመረጠ፣ ፍቅርና አንድነትን የወደደ ብሎም ለነጻነትና እኩልነት፣ ለብልጽግናና ሰብዐዊነት የቆመና የቆረጠ ሁሉ ተደማሪ ሊሆን ይችላል።

የመደመር ሜዳው ሰፊ፣ እድሉ ብዙ መንገዱም ልዩ ልዩ ነው። ስለዚህም አልፈልግም አሻፈረኝ ከሚልና ለግል ጥቅሙና አላማው ማስፈጸሚያ ፈልጎ ልደመር ከሚል በቀር የመደመር በር ለሁሉ ክፍት ነው።

ህጻናንት በፍቅራቸው፣ ወጣቶች በብርታታቸው፣ ጎልማሶች በልምዳቸው አዛውንቶችም በጥበባቸው ሊደመሩ ይችላሉ። ነጋዴ በገንዘቡ፣ መምህር በእውቀቱ፣ ገበሬ በምርቱ፣ ዳኛ በፍትሁ፣ ከያኒ በጥበቡ ሊደመር ይችላል።