ከህግ አውጭው፣ ከህግ ተርጓሚው እና ህግ አስፈፃሚው ቀጥሎ እንደ አራተኛ መንግስት የሚጠቀሰው ሚዲያ አገራትን በዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ እስከማድረግ ደርሷል። በሌላ በኩል ደግሞ ሚዲያን መግራትና በአግባቡ መጠቀም ያልቻሉ አገራት ፈራርሰዋል።
ሚዲያዎችን ሀሳቦች በነፃነት የሚንሸራሸሩባቸው በማድረግ በጅምር ላይ ላለው አገረ መንግስት ግንባታችን ቁልፍ ሚናቸውን እንዲወጡ በተለይም ከለውጡ ጀምሮ አበረታች ስራዎች ተከናውነዋል።
የህዝብ ሀብት የሆኑ ሚዲያዎች ሪፎርሞች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን ጭምር የቦርድ አባላት በማድረግ አካታች እርብርብ ተጀምሯል።
ከሚዲያ ነፃነት ጎን ለጎን የሚዲያ ተጠያቂነትም መኖሩን የሚዘነጉ አካላት የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም በማዋል ህዝባችን ላይ መከፋፈልን የሚሰብኩ የጥላቻ መልዕክቶቻቸውን በስፋት ማስተላለፋቸውና አሁንም የሚያስተላልፉ መኖራቸው ከህዝባችን የተደበቀ አይደለም።