በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በ3 ወራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና ካቢኒያቸው በተገኘበት እየተገመገመ ይገኛል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እንደገለጹት የሀዋሳ ከተማ ለነዋሪዎች የምትመች እና ሁለንተናዊ ብልፅግናዋ የተረጋገጠ እንድትሆን የተሻለ የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ በልዩ ትኩረት እየተመራ እንደሚገኝ አንስተዋል ።
የህዝብን አንገብጋቢ ጥያቄዎች ለመመለስ በሚያስችል መልኩ የከተማውን አመራር እንደ አዲስ በማደራጀት በርካታ ተግባራት ላይ ውጤት እያመጣ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድሩ በማንሳት ለከተማው ሁለንተናዊ ዕድገት እና ልማት አመራሩ በጊዜ የለኝም መንፈስ እንዲንቀሳቀስ መልዕክት አስተላልፈዋል።