ብልፅግና ፓርቲ የብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ መዋቅርን ማዕከል ያደረገ አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት አበክሮ እየሰራ ነው።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በሁለንተናዊ ብልፅግና የአፍሪካዊ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ፓርቲያችን ሲነሳ የሀገራችንን ህዝቦች የአሁኑንና የመጭውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎትን ማዕከል ያደረገ አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት ነው።
ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናችን ሁሉን አቀፍ ማህበረሰብ ለመገንባት የምናደርገውን ጥረት የሚደግፍና አንድ የኢኮኖሚና የፓለቲካ ማህበረሰብ የመገንባት ትልም ያለው እንዲሆን ይሰራል። ስለሆነም በኢኮኖሚ ፕሮግራሙ የብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ መዋቅር የመገንባት፣ ሀብት ፈጠራን የሚያሳድግ ዕውቀት መር የኢኮኖሚ ስርአት፣በከተማ ልማትንና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ያማከለ እና ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ልማትና ምርታማነትን መሰረት ያደረገ የኢኮኖሚ ስርአት እየገነባ ይገኛል።